የመረጃ ምንጮች

211info.org ወይም 211። ለመኖሪያ ቤት፣ ለፍጆታ ዕቃዎች፣ ለሸቀጣሸቀጦች፣ ለልጆች እንክብካቤ እና ለሌሎችም ለመክፈል እርዳታ ያግኙ።

Healthcare.oregon.gov ወይም 1-855-268-3767። የጤና ሽፋን ካጡ ወይም ከሌለዎት፣ ለነፃ ወይም ለዝቅተኛ ዋጋ የጤና እቅድ ብቁ ሊሆኑ ይችላሉ።

የሥራ ገበያ መረጃ። የኦሪገን የሰራተኛ ገበያ መረጃ ስርዓት (Oregon’s Labor Market Information System) ወቅታዊ የሥራ ቅጥር መረጃዎችን፣ ልዩ ሪፖርቶችን እና ወቅታዊ የሥራ ዝርዝሮችን ያቀርባል። የሥራዎች እና የሥራዎች መስክ ትር ደመወዞችን፣ የታቀደ የሥራ ዕድገትን እና ከ 700 በላይ ለሚሆኑ ሥራዎች ክፍት የሥራ ቦታዎችን ለማግኘት ያስችልዎታል። ለበለጠ መረጃ www.qualityinfo.org ን ይጎብኙ።

የኦሪገን የቤት ባለቤትነት መረጋጋት ተነሳሽነት ከ 2011 ጀምሮ፣ ከ 16,000 በላይ የኦሪገን ቤተሰቦች ቤታቸውን እንዲያኙ ረድተናል። የገንዘብ ሁኔታዎ አሁን የተለወጠ እንደሆነ ወይም ለተወሰነ ጊዜ ሲታገሉ ከነበረ፣ እኛ ለእርስዎ እዚህ ነን።

አስተማማኝ + ጠንካራ ኦሪገን እርስዎ፣ ቤተሰብዎ እና ማህበረሰቦቻችን ጠንካራ ሆነው እንዲቀጥሉ ኮቪድ-19 ን በደህና ለማለፍ የመረጃ ምንጮችን ያግኙ።