541VETS በኦሬጎን ገጠር ውስጥ ለሚኖሩ አርበኞች፣ የትዳር ጓደኞቻቸውና ሌሎች ሽፋን የተሰጣቸው ሰዎች ስልጠናና የስራ ቅጥር ድጋፎችን የሚሰጥ የዲጂታል ቤተ መጻህፍት ነው።
541VETS የተዘጋጀው እያንዳንዱ በገጠር የሚኖር አርበኛ፣ ብቁ የሆነ የአርበኛ የትዳር ጓደኛ እና ሌሎች ሽፋን የተሰጣቸው ሰዎች አካላዊ የመገኛ ቦታቸው የትም ይሁን የት ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያላቸው፣ ድጋፍ ሰጪ የሥራ ቅጥር ምንጮችን በዕኩል ደረጃ ማግኘታቸውን ለማረጋገጥ ነው። እንዲሁም የድጋፍ ምንጮቹን ሰውን ባማከለ፣ ግላዊ መልኩ ማቅረብ ደንበኛን በወቅቱ ለእርሱ ምርጥ የሆኑ የድጋፍ ምንጮችን እንዲመርጥ ያስችለዋል።
የዲጂታል ቤተ መጻህፍቱ በአሁኑ ወቅት ታክቲካዊ የሙያ እቅድ ዝግጅት ቪዲዮዎች ባህሪያትን የሚይዝ ሲሆን ተጨማሪ የስልጠና ቪዲዮዎችን፣ ፖድካስቶችን፣ የማህበረሰብ፣ የንግድና የሙያ ማብራሪያዎችን እንዲያካትት ተደርጎ እያደገ ይሄዳል።
ታክቲካዊ የሙያ እቅድ ዝግጅት ክፍል 1: መግቢያና ጠቅላላ ዝግጁነት (in English)
የሥልጠና ቪዲዮዎች (in English)
- ክፍል 01 – መግቢያና ጠቅላላ ዝግጁነት
- ክፍል 02 – የወታደር ንግግርን መተርጎም
- ክፍል 03 – የሽፋን ደብዳቤዎች
- ክፍል 04 – የተግባር የትምህርትና የስራ ልምድ ዝርዝር
- ክፍል 05 – ጥምር የልምድ ዝርዝሮች
- ክፍል 06 – የኦንላይን ምንጮች
- ክፍል 07 – የተደበቀ የስራ ገበያና አውታር
- ክፍል 08 – መረጃ ሰጪ ቃለ መጠይቆችና የሥራ ከለላ
- ክፍል 09 – ልምምዶችና የሥራ ላይ ስልጠና
- ክፍል 10 – የመስመርና አካባቢ ሪኮን
- ክፍል 11 – የአለባበስ ደንብና የግል ንጽህና
- ክፍል 12 – ቃለ መጠይቆች: የገጽ ለገጽ፣ ፓናልና ቨርቹዋል
- ክፍል 13 – ስራውን ይጠይቃሉ!
የሰነድ ናሙናዎች (in English)
የሰነዶች ቅደም ተከተል (in English)
የንግድ መረጃዎች (in English)
- የHIRE Vets Medallion ፕሮግራም (HVMP)
- የአርበኞች አስተዳደር - ልዩ የሥራ ቅጥር ማበረታቻ ፕሮግራም (SEI)
- የሥራ እድል የግብር ብድር (WOTC)
Head Space and Timing ጋዜጣ (በእንግሊዝኛ)
The Business Up-Brief ጋዜጣ (በእንግሊዝኛ)
የስቴቨንስ ማሻሻያ እውቅና
ለስራዎች የመንግስት እርዳታ ለአርበኞች/Jobs for Veterans' State Grant (JVSG) በዩኤስ የሰራተኛና አሰሪ መምሪያ፣ በአርበኞች የሥራ ቅጥርና ስልጠና (USDOL-VETS) በኩል 100% የፌደራል የገንዘብ ድጋፍ ይደረግለታል። እርዳታው ጠቅላላ ድምሩ $2,429,678 የሆነ ስጦታ አካል ሲሆን መንግስታዊ ካልሆኑ ምንጮች የሚደረግለት ድጋፍ 0% ነው።
ለስራዎች የመንግስት እርዳታ ለአርበኞች/Jobs for Veterans' State Grant ለአርበኞች የስራ ዕድሎችን ለመጨመር ዓላማ ወደ ንግዱ ማህበረሰብ ስምሪት ለማድረግና በማስተዋወቅ ጥረቶች ላይ ለመሳተፍ የፌደራል የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል። እርዳታው በተጨማሪም ስራ ለመቀጠር ከፍተኛ እንቅፋቶች ለሚያጋጥሟቸው አርበኞችና ብቁ የሆኑ ሰዎች በግል ለሚቀርቡ ከሙያና ስልጠና ጋር ተያያዥ አገልግሎቶች የገንዘብ ድጋፍ ይሰጣል።