ቅሬታዎች

ቅሬታ ያስመዝግቡ

የሚከተሉትን በተመለከተ ቅሬታ አልዎት፡

  • የኦሬጎን የስራ ቅጥር መምሪያ (Oregon Employment Department) ወይም WorkSource የኦሪገን ማዕከል የስራ ቅጥር አገልግሎቶችን በተመለከተ?
  • ከስራ ቅጥር ጋር ተያያዥ ሕግ?
  • በኦሬጎን የስራ ቅጥር መምሪያ (Oregon Employment Department) ወይም WorkSource የኦሪገን ማዕከል የተመሩበትን ቀጣሪ ወይም ስራ በተመለከተ?
መብቶችዎ እንደተጣሱ፣ ሊከፈልዎት የሚገባ ደመወዝ እንዳልተከፈልዎ፣ ጤናዎና ደህንነትዎ አደጋ ላይ እንደወደቀ፣ ወይም በስራ ቦታ ላይ የመገለል/አድልዎ ሰለባ እንደሆኑ ካመኑ ቅሬታ ማስመዝገብ ይችላሉ። ቅሬታዎ በቀሰጣሪዎ፣ በኦሬጎን የስራ ቅጥር መምሪያ (Oregon Employment Department)፣ WorkSource የኦሪገን ማዕከል የተወሰድ ወይም ያልተወሰዱ እርምጃዎችን መያዝ፣ ወይም በሰራተኛ ሀይል የፈጠራና እድል ሕግ የገንዘብ ድጋፍ በሚደረግለት ተሳትፎዎ ምክንያት የሚቀርብ መሆን አለበት።
 

የሚከተሉትን በማድረግ እንረዳዎታለን፡
  • በኦሬጎን የስራ ቅጥር መምሪያ (Oregon Employment Department) ወይም WorkSource የኦሪገን ማዕከል ሪፈር የተባሉባቸውን ልዩ ስራዎች፣ ቀጣሪዎች ወይም የስልጠና ፕሮግራሞችን በተመለከተ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በመመርመር።
  • በኦሬጎን የስራ ቅጥር መምሪያ (Oregon Employment Department) ወይም WorkSource የኦሪገን ማዕከል የሚቀርቡ ፕሮግራሞች ወይም አገልግሎቶች አቅርቦትን በተመለከተ የሚቀርብ ቅሬታን በመመርመር።
  • የኦሬጎን የስራ ቅጥር መምሪያ (Oregon Employment Department) ቅሬታዎን የማየት ስልጣን የማይኖረው ከሆነ ቅሬታዎን ለሚመለከተው ኤጀንሲ በመምራት።
ቅሬታዎን የት እና እንዴት እንደሚያስመዘግቡ ለማየት የኦሬጎን የስራ ቅጥር መምሪያ (Oregon Employment Department) ድረገጽ የዕኩል ዕድል ገጽን (Equal Opportunity page)፣ ወይም የES የቅሬታ ስርዓት (ES Complaint System) ገጽን ይጎብኙ፣ ወይም የአካባቢዎን WorkSource የኦሪገን ማዕከል ያነጋግሩ።
 
በቀጣሪ ላይ ለሚቀርቡ የእኩል ዕድል እና የአድልዎ ቅሬታዎች እባክዎ BOLIን እና/ወይም የእኩል የቅጥር ዕድል ኮሚሽንን (Equal Employment Opportunity Commission (EEOC)) ያነጋግሩ።

ለደመወዝ፣ ልዩ ክፍያ ወይም የመኖሪያ ቤት አድልዎ ቅሬታዎች BOLIን ያነጋግሩ።

ስለ የስራ አጥነት መድን ዋስትና ጉዳይዎ በተመለከተ ቅሬታ ካልዎ በውሳኔ ደብዳቤዎ ላይ የተገለጹትን መመሪያዎች ይከተሉ፣ ወይም የስራ አጥነት መድን ዋስትናን በስልክ ቁጥር 877-345-3484 ወይም በContact Us የኦንላይን ቅጽ (Contact Us online form) ያነጋግሩ።